Songtexte.com Drucklogo

Liela Lalay Songtext
von Abdu Kiar

Liela Lalay Songtext

ሌላ ላላይ - አብዱ ኪያር
ምፈልገው ፍቅር ባንቺ ተሳካና
መንፈሴም አረፈ ከሀሳብ ዳነና
ሽልማቴ ያልኩሽ በሌላም አይደለም
ከሱ ያገኘሁሽ ፍቅሬ ነሽ ዘላለም

ቃል ገባሁ በሰው ፊት ይኸው ባደባባይ
ካንቺ ሌላ ላላይ
የሱ ፍቃድ ሆኖ አንቺን አግኝቻለው
ምን እፈልጋለው


መቼና እንዴት ሆነ አላውቀው ለራሴ
ገና ባይኔ ሳይሽ ፈገግ ይላል ጥርሴ
እስከማውቀው ድረስ እስከማስታውሰው
እንዳንቺ ያስደሰተኝ አላውቅም አንድ ሰው

ቃል ገባሁ በሰው ፊት ይኸው ባደባባይ
ካንቺ ሌላ ላላይ
የሱ ፍቃድ ሆኖ አንቺን አግኝቻለው
ምን እፈልጋለው

ሳወጣና ሳወርድ ምንም ያላየሁት
ሳስብ ኖሬ ኖሬ ፈልጌ ያጣሁት
ድንገት ባጋጣሚ በተዓምር ነው እንጂ
ፍቅር በእቅድ የለም አየሁ እድሜ ላንቺ


ቃል ገባሁ በሰው ፊት ይኸው ባደባባይ
ካንቺ ሌላ ላላይ
የሱ ፍቃድ ሆኖ አንቺን አግኝቻለው
ምን እፈልጋለው
ኦሆሆሆሆሆ

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Beliebte Songtexte
von Abdu Kiar

Ähnliche Artists

Fans

»Liela Lalay« gefällt bisher niemandem.