Songtexte.com Drucklogo

Negen Zare Sira Songtext
von E on the Beat

Negen Zare Sira Songtext

መቼም አይቀርም ጊዜው መሄዱ
ምን ሰራህ ዛሬ ለነገ እንዲቀና መንገዱ
መኖር ከፈለክ ስኬታማ ሁነህ
መጋጠም አለብህ ውጣ ውረዱን ደፍረህ

ዛሬ ላይ ቆመህ ስታሰላ ትናንትን
ምን ሰርተህ ነበረ ለዛሬው ራስክን
የት ደረጃ ላይ ነህ አሁን በዚህ ሰዓት
ለዚህስ ያደረሰህ ምን ሰርተህ ነው ትናንት
ስኬታማ ሰዎች ኑሯቸው የታደለ
ከበስተጀርባቸው ትልቅ ልፋት አለ
በአንፃሩ ደግሞ ተቃራኒ የሆኑት
ትናንታቸውን ተኝተው ነው ያሳለፉት


ልመልሳችሁ ወደ ግል ህይወቴ
የሆነ ነገር አወጉኝ አባቴ
ብለውኝ ነበረ አንድ ነገር
የማይጠፋኝ ሞቼም ብቀበር
"ዛሬ ላይ በደንብ ስራ የኔ ልጅ
መውደቂያህ እንዳይሆን በሰው እጅ
እመነኝ ታመሰግነኛለህ
ነገን ሁነህ ሲሳካ ህይወትህ"

ስለዚህ ጎበዝ ተነስ አትቀመጥ
የነገ ህይወትህ ላይ አታላግጥ
መኖር ካለብህ ተደስተህ ኑር
ለመደሰት ደግሞ ራስህን አክብር
ራስን ማክበር ከየት ይጀምራል
ለነገ ስትል መጣጣር ይኖራል
ስለዚህ አትሸወድ ወንድም አደራ
አንድ ነገር አስታውስ ነገን ዛሬ ስራ!

ከተራራው ጫፍ ላይ ስደርስ አየሁት
እንደተቃረብኩም ራሴን ጠየኩት፣ አሰላሰልኩት
"ያኔ ባልጀምረው ያኔ ልጅ እያለሁ
ገና የት ነበርኩኝ እዚህ ባልደረስኩኝ"
አልኩኝ እና፣ ቀና አልኩኝ
ፈጣሪዬን፣ አመሰገንኩኝ
"አመሰግናለሁ!"


ወጣትነትህ እንዲበራ
አሁን ላይ ተግተህ በደንብ ስራ
ስራህን ግን በምርጫህ አርገው
ተገደህ ሳይሆን ወደህ ስራው!
(ወደህ ስራው!)

Songtext kommentieren

Log dich ein um einen Eintrag zu schreiben.
Schreibe den ersten Kommentar!

Fans

»Negen Zare Sira« gefällt bisher niemandem.